Our Whatsup Group is Open.

ውድ የኢትዮጵያን ማህበር በአውሮፓ አባላትና ወዳጆች
እንደሚታወቀው ከቀናት በፊት በሰጠነው ማሳሰቢያ መሠረት የማህበራችንን ውስጣዊ የስራ አካሄዳችንን ከመረመርንና አንዳንድ ማሻሻያዋችን ለማድረግ በገባነው ቃል መሰረት ፣ እንቅስቃሴያችንን በብዛት ሳይሆን ፣በጥራት ፣ በመጠላለፍ፣ ሳይሆን በመተሳሰብ ፣ በክፋት ሳይሆን በቅንነት ፣ በበጎነት የምንራመድበትን ብዙ የደከምንለትን የማህበራችንን የዋትስአፕ ግሩፕ በነባርና ህጋዊ ስምና ሎጎ ከዛሬ ጀምሮ ተመልሰን የመጣን መሆናችንን በደስታ እናሳውቃለን። ለህዝባችን ለወገናችን ከጎኑ ቆመን ድምፅ የምንሆንለት፣ ለሀገራችን መከታ ለውጭም ሆነ ለውስጥ ወራሪዋች ለአፍታ የማንተኛ መሆናችንን የምናስመሰክርበት መድረካችንን በነቃ ተሳትፎ እናጎለብተው ዘንድ በአክብሮት እየጠየቅን ። ለማህበሩ ዋትስአፕ ግሩፕ ጊዛያዊ የዕረፍት ወቅት ስሜታችሁን፣ ፍላጎትና ምክራችሁን በስልክ ሆነ በተለያየ መልኩ የገለፃችሁልን የማህበሩ ወዳጆች ልባዊ ምስጋናችን ይድረሳችሁ እያልን በአንፃሩ ይህንን አጋጣሚ በሌላ መልኩ የማህበራችንን ስምና ሎጎ በመጠቀም ለተደራጃችሁ አካላት ከስህተታችሁ ቶሎ ብላችሁ እርምት ትወስዱ ዘንድ ተደጋጋሚ ምክራችንን እንለግሳለን። በማህበሩ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ከተወሰኑ ውሳኔዋች ውስጥ የዲሲፕሊን ኮሚቴ የሚያውጣቸው የእርምት ውሳኔዋች ይገለፃሉ።
ኢትዮጵያንና ህዝባችንን ፈጣሪ ይጠብቅ ሞት ለህወሀትና ለአጨፋሪዋቻቸው በብሔርና ክልል ያልተከፋፈለች ኢትዮጵያን ለመገንባት አንድ እንሁን።

To join our whatsaup group, click on the link below.

ከሰላምታ ጋር፣
የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ
Join Our Facebook Group

https://www.facebook.com/ethiodiasporaeurope

To become a member of our Association, please click fill up the form HERE.

About expeder

Check Also

ከኢትዮጵያዉያን ማህበር በአዉሮፓ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

PressRelease-AMHARIC- by A.E.E-March 23-2024

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

+ 23 = 30