Rising Ethiopia – Ambassador Mulu Solomon

ኢትዮጵያን በኢትዮጵያውያን እናስተዋውቅ በሚል ለሁለት ወራት የሚቆይ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻ ይፋ ሆነ
*********************
ኢትዮጵያን በኢትዮጵያውያን እናስተዋውቅ በሚል ለሁለት ወራት ከታኅሣሥ 21 ቀን 2013 እስከ የካቲት 14 ቀን 2013 ዓ.ም. የሚቆይ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻ ይፋ ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የቱሪዝም ሀብት፣ የተለያዩ ውሎችና የኢንቨስትመንት እድሎች ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ ዳያስፖራና ኤምባሲዎችን በማንቀሳቀስ በማኅበራዊ ድረ ገጽ የሚካሄደው ዘመቻ ገፅታን ለመገንባት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በዩናይትድ ኪንግደም ነዋሪ የሆኑት ዶ/ር በላቸው ተስፋ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለንደን ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በመነጋገር ያቀረቡት ሐሳብ ተቀባይነት በማግኘቱ የማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻው ተጀምሯል፡፡
በበይነ መረብ በተካሄደው የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እንደተናገሩት፣ የቱሪዝም ሀብታችንን ይበልጥ በማስተዋወቅ ተደራሽነታቸውን በማስፋት አገራችንን የሚጐበኙ ቱሪስቶችን ቁጥር በመጨመር ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማበርከት የማኅበራዊ ድረ ገጽ ዘመቻው አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው፡፡
በተለያየ የዓለም ክፍል የሚኖረው እና በሥራና በተለያዩ ምክንያቶች ከተለያዩ የውጭ ማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር የሚገናኘው ዳያስፖራ በዓለም አቀፍ ደረጃ በማንቀሳቀስ በቅብብሎሽ የሚከናወን የማስተዋወቅ ሥራ ተደራሽነቱ ሰፊ ነው፡፡
በመሆኑም የአገሪቱን ገጽታ የበለጠ ለመገንባት እና በኮቪድ 19 በኋላ በርካታ የውጭ ቱሪስቶች አገሪቱን እንዲጐበኙ ለመሳብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡
ዳያስፖራው ከአገሩ ጋር ያለውን ትውስታ እና ትስስር በመጨመር በዘመቻው ለመሳተፍ ያለውን ፍላጐት የሚያጠናክር እና ትልቅ እድልም የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት መንግሥትም ዘርፉን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በመገንባት፣ ከዚህ ቀደም የነበሩትንም በማስፋትና የተለያዩ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችን በማከናወን በርካታ እንቅስቃሴዎች በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የአገራችን ክልሎች እያከናወነ ነው፡፡
ይሁን እንጂ በመንግሥት በኩል ብቻ እየተከናወነ ያለው ተግባር አገሪቱን ለማበልጸግ በቂ ስለማይሆን ዳያስፖራው በራሱ ተነሣሽነት እንዲሁም ያሉትን እድሎች አቅም ላላቸው የውጭ አገር ባለሀብቶች ግንዛቤ በመፍጠር በአገሩ ልማት ላይ እንዲሳተፍ አምባሳደር ተፈሪ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በበይነ መረብ ውይይቱ የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ተወካይ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ፣ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ በአውሮፓ የሚገኙ የኢትዮጵያ አምባሳደሮች፣ የቱሪስት አስጎብኚ ድርጅት ተወካዮች ተሳትፈዋል።
የቪዲዮ መረጃዎቻችንን ለማግኘት ትክክለኛውን የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
በምስል የሚገኙ መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የኢንስታግራም ገፃችንን ይከተሉ
አጫጭርና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ

https://www.facebook.com/watch/?v=1361652727522626

About expeder

Check Also

ከኢትዮጵያዉያን ማህበር በአዉሮፓ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

PressRelease-AMHARIC- by A.E.E-March 23-2024

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

78 − = 70