የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ የመተዳደሪያ ደንብ

የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ የመተዳደሪያ ደንብ

ምዕራፍ አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌ

አንቀጽ1. ስያሜ

ይህ ማህበር “የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ ተብሎ ይጠራል።

አንቀጽ 2 አድራሻ፣መቋቋምና ተልኮ

2.1.የማህበሩ አድራሻ በጀርመን በፍራንክፈርት ከተማ ነው።
2.2. ማህበሩ በመላው አውሮፓ ቕርንጫፎች ይኖሩታል::

2.2.ማህበሩ በጀርመን(የአውሮፓ ) የማህበራት ህግና ደንብ መሰረት ማህበራዊ ዓላማዎችን ብቻ ተግባራዊ የሚያደርግ ድርጅት ነው
2.3.የማህበሩ ንብረት የማህበሩን ህገደንብ የሚያክብሩ ዓላማዎችን ማስፈጸሚያ ብቻ ይውላል.
2.4.ማህበሩ ከማንኛዉም ኢትዮጵያ ዉስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ዉጪ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካና የዘር ድርጅቶችና ማህበራት ገለልተኛ ነው::
2.5.ማህበሩ በጀርመን (በአውሮፓ ) ሕግ መሰረት ተቋቁሞ፣ ለትርፍ የማይሰራ ማህበር ነው።
2.6.ማህበሩ የተቋቋመው ላልተወሰነ ጊዜ ነው።

ምዕራፍ ሁለት

አንቀጽ 3 ዓላማ:.

3.1.የዜጎች ሠብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ሙሉ በሙሉ የተከበሩባት የህግ ልዕና እንዲረጋገጥ መታገል
3.2. በዜጎች መሃል እኩልነት እንዲሰፍን፣ የብሄር ብሄረሰቦቿ መብቶች እንዲረጋጡ፣ መተማመን እንዲጎለብት ለጋራ አገር በጋራ መቆም እንዲጠናከር መስራት
3.4. መንግስት የህዝብንና አገርን አደራ በመቀበል የዜጎችን እምባ የሚያብስ የእድገት መሰላል ሆኖ መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት መንፈስ እንዲሰራ ለማበረታታት
3.5 ዜጎች የኢትዮጵያን ብሄራዊ ጥቅሞች በጋራ እንዲገነቡ፣ እንዲጠብቁና እንዲያስከብሩ ሁለንተናዊ ድጋፍ ለመስጠት
3.6. በውጭ አገር የሚኖረው ኢትዮጵያዊ በዘርና በሃይማኖት ሳይከፋፈል የህዝባችን ቋሚ ደጀን በመሆን ለአገራዊ እድገታችን በጋራ እንድንሰራና የሚቻለንን አስተዋጽኦ ለማድረግ::
3.7. በኢትዮጵያ ፈጣንና ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ እድገት ለማረጋገጥ፣ የሃብት ፍሰት፣የእውቀት ሽግግርና የተክኖሎጂ ውጤቶችን ለማቅረብ ጥረት ማድረግ ::
3.8 ዜጐች ለሀገራቸው ፍቅር እንዲኖራቸው፣ ለጋራ እድገታቸው በተባበረ ጉልበት፣ እውቀት፣ ለዘላቂና አስተማማኝ ዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲሰሩ ለማበረታታት::
3.9.ተፎካካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች የነገ አማራጭ፡መንግስት የመሆን እድሉን ለማግኘት ህዝብን በጎጥ የመከፋፈል መርዝን ከመርጨትና እልቂትን ከመደገስ ተቆጥበው በታላቅ አገራዊ የሃላፊነት መፈስ እንዲራመዱ ለማበረታታት
3.10.ፍትሃዊና ርታዐዊ ምርጫ ብቸኛው የስልጣን ቅብብሎሽ መሆኑን በመቀበል ሁሉም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች ተደማምጠውና ተከባብረው ለዴሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲሰሩ በተፈተኑ የዓለማችን ተሞክሮዎች ለማገዝ ::
3.11. የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ በራሱና በወረሰው መልካም ነገር የኩራት መንፈስ እንዲያዳብር ጥረት ማድረግ፣ የነገ ተስፋውን በሚያጨልሙ የዘር ቡድኖች ተከፋፍሎ ከመናቆር ተቆጥቦ እራሱን በእውቀትና ክህሎት በማነጽ፣ የበለጸገች ደሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን በመፍጠርና የአገር ተረካቢነቱን ተልኮ በክብር እንዲወጣ ለማደፋፈር
3.12. የአባይን ግድብና ሌሎች ተፈጥሮአዊ ሃብቶቻችንን መጠቀም ልዑላዊ መብታችን በመሆኑ በማንም ለድርድር እንዳይቀርቡ ተባብሮ ለመስራት የዕውቀት የገንዘብ የቁሳቁና የድፕሎማሲ ሁለንተናዊ ድጋፍ መስጠት
3.13.ሚዲያ የመረጃ ምንጭ እንደመሆኑ የድምጽ የሕትመት የምስል ተቋሞቻችን ና በመስኩ የተሰማሩ ጋዜጠኖችና ባለሞያዎች ለማንም ያልወገነ እውነተኛ የመረጃ ምንጭ እንዲሆኑና አገርን ከጥፋት ህዝብን ከ እልቂት እንዲታደጉ ለማስቻል ሁለንተናዊ ድጋፍ መስጠት
3.14. በዲያስፖራ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ሳንክፋፈል እኔም በአገሬ ጉዳይ ያገባኛል መንፈስ ሁለንተናዊ አቅሞቻችችን በማስተባበር ለኢትዮጵያችን እንድናበረክት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ
3.15. አገራዊ አንድነትዋ የተጠበቀ የህዝቦቿ ልዑላዊነት የተረጋገጠ፣ ዘላቂ ሰላም የሰፈነባት፣ ጠንካራ ማህበራዊ ኢኮኖሚ የተገነባባትን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመፍጠር የሚካሄደውን ትግል ለማገዝ::

ምዕራፍ ሶስት

አንቀጽ 4 ተግባር

የማህበሩ ተግባራት

4.1.ማህበሩ ለማህበራዊ፣ ለባህላዊና ሰብዓዊ ዓላማዎች የቆመ ሲሆን በአንቀጽ 3 የተጠቀሱትን አላማዎች ለማሰጸም የሚከተሉትን ዝርዝር ተግባራት ያከናውናል.
4.2.ማህበሩ የኢትዮጵያን ህዝብ የተለያዩ ባህላትና ቋንቋዎች ወግና ትውፊቶች በአውሮፓ አገሮች በማስተዋወቅ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው አገሮች በንቃት እንዲሳተፉ ይሰራል::
4.3፣ ከጀርመን መንግስት ( በአውሮፓ ) ከሚገኙ መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችና መንግስታዊ ያልሆኑ የሲቪክ ማህበራትና የሃይማኖት ተቋማት ጋር በመገናኘት ለኢትዮጵያ አገራችን ሁለንተናዊ ድጋፍ እንዲሰጡ ይጥራል፣..
4.4.በአውሮፓ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ን በማስተባበር በአገር ውስጥ እየተካሄደ ላለው የአገር ግንባታ የሞራል ፣ የፋይናንስ ፣የቁሳቁስ እርዳታና የዕውቀት ሽግግግር ንቁ ሆነው እንዲሳተፉ ማድረግ
4.5.የማህበሩ የገንዘብና የዝግጅት ኣቅም በፈቀደ ጊዜ የኢትዮጵያንና ታሪካዊና ሃይማኖታዊ በዓላትን በማዘጋጀት ህብረተሰቡ ተሰብስቦ በጋራ እንዲያከብር ያደርጋል::
4.6.የማህበሩ የኣባላት ኣቅም ሲዳብርና ሁኔታዎች ሲፈቅዱ የተለያዩ ዘርፎች ኮሚቴዎችን ያደራጃል::
4.7.በኢትዮጵያና በአውሮፓ የተፈጥሮ አደጋዎች (የዉሃ መጥለቅለቅ የድርቅ የመሬት መንቀጥቀጥና የመሳሰሉት) ሲደርሱ ማህበሩ የኢትዮጵያንና የአውሮፓ መንግስታትን ፣መንግሥታዊ ያልሆኑ የግልና የቤተክርስቲያን እርዳታ ሰጪ ድርጀቶችን በማስታባበር እርዳታ ለማሰባሰብ ይጥራል. የማህበሩ የገንዘብ አቅም ከፈቀደ ከካዝናው የገንዘብ እርዳታ ይለግሳል::የሚለገሰው መጠን የሚወሰነው በጠቅላላ ጉባዔው ነው::
4.8. ማህበሩ በኢትዮጵያ፣ በጀርመንና በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ የሰባዊ መብት አስከባሪ ደርጅቶች ጋር ግንኙነት ይፈጥራል. ኢትዮጵያ ዉስጥ የሰብዓዊ መብት በሚጣስበት ጊዜ ማህበሩ ከላይ ለተጠቀሱት ድርጅቶች ሁኔታውን ያስታውቃል ሰላማዊ ሰልፍ ይጠራል፣ ፊርማዎችን ያሰባስባል ጋዜጣዊ መግለጫዎችንም ይሰጣል::
4.9.በጀርመን (በአውሮፓ )ውስጥ ህገውጥ ድርጊቶችና በዘረኝነት መንፈስ ተነሳስቶ የሚፈጽም ጥቃት ሲፈጸም ከሰብዓዊ ደርጅቶች ጋ በመተባበር ከጋዜጣዊ መግለጫ እስከ ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ድረስ የሚዘልቅ እንቅስቃሴ ያደርጋል::
4.10.የማህበሩ የገንዘብና የሰው ሃይል ኣቅም ሲፈቅድ የማህበሩ ኣባላትና ኢትዮጵያዉያን የሚሳተፉበት በራሱ ስም መጽሄት ያዘጋጃል፣ መጽሄቱ የሚወጣበትን ጊዜ ኣንደኣስፈላጊነቱ ይወሰናል::
4.11.ማህበሩ በወቅታዊ የአገራችንና የዓለም ዓቀፍ ሁኔታዎች ዙሪያ ሴሚናሮች፣ የኮንፈረንሶችንና ሲምፖዚዬሞችና መድረክ በማዘጋጀት የኢትዮጵያዉያንና የጀርመን (አውሮፓ ሕብረት) የፖለቲካ፣ የታሪክና የኢኮኖሚ ምሁራን፣ ሌሎች ባላሙያዎችና የሙያ ማህበራት ተወካዮችን ወዘተ. ጋብዞ በጀርመን(በአውሮፓ ሕብረት) የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን በሃገራቸዉና በጀርመን ሃገር ስላለዉ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲያዉቁና ኣመለካከታቸዉን እንዲያዳብሩ ያደርጋል
4.12. ማህበሩ በአገራችን የሚከናወናውን ለውጥ እየተከታተለ የተሻለ ነገር ሲሰራ በማድነቅ ጥፋቶች ሲታዩ አመራሩ እየገመገመ መግለጫ ይሰጣል፣ ጋዜጣዊ መግለጫዎች ያወጣል
4.13. ማህበሩ ዓላማዎችን ለማሰፈጸም እንዲረዳው የዲጂታል ሚዲያን በመጠቀም ድረገጽ ፣ማህበራዊ ሳይቶችን ያደረጃል ፣አቅም በፈቀደ መጠን የድምጽ ፣ የምስልና የህትመት ውጤቶችን ያሰራጫል::
4.14. የመረጃ አያያዝ ቅርፆችን መቅረጽ ፣ የተደራጀ መረጃ በወቅቱ እና በአግባቡ መያዝ፣ መሰረታዊ ተግባራት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት::
4.15. ለማህበሩ አባላት በየወቅቱ መረጃ በማስተላለፍ ተሳትፎቸውን የማሳደግ የውቀትና የልምድ ሽግግርን ማጠናከር።
4.16. በአገራችን እየተካሄደ ያለውን ዴሞክራሲያዊ የለውጥ ሂደት እንዳይደናቀፍ የለውጥ ኃይሉ የሚያደርጋቸውን ክንውኖች በተግባር ማበረታታትና በሚቻለው ሁሉ ድጋፍ እንዲያገኝ መርዳት::
4.17. የአባይ ግድብ ግንባታ የአገራችን ዘላቂ እድገት ዋስትናችን በመሆኑ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምንኖር ዜጎች እጅ ለእጅ ታያይዘን ሁለንተናዊ ድጋፍ ያገኝ ዘንድ የተጠናክረ ስራ መስራት
ታሪካዊ አሻራችንን በማኖር የዜግነት ግዴታን በክብር ለመወጣት መንቀሳቀስ።
4.18.የአባይ ግድብ እንዳይሳካ የግብጽ መንግስትና የዐረብ ሊግ የልማት ጎዞአችንን ለማደናቀፍ የሚሸርቡትን ደባ ሴራ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማጋለጥ የተቀናጀ ዘመቻ ማካሄድ!

ምዕራፍ አራት

አንቀጽ 5. አባልነት

5.1. አባል ስለመሆን፣
5.1.በአውሮፓ አህጉር የሚኖር ዕድሜው 18 በላይ የሆነ፣ለህጋዊ ተጠያቂነት የሚበቃ ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ፣
5.2 የማህበሩን ደንብና ሕግ የተቀበለና ለማህበሩ ዓላማዎች ተግባራዊነት የሚቆም ማንኛውም ሰው አባል መሆን ይችላል።
5.3.1.ከኢትዮጵያውያን ጋር በጋብቻና በማደጎ ትስስር ያላቸው የሌላ ሀገር ዜጎች የክብር አባል መሆን ይችላሉ::
5. 3.2.የማህበሩ የክብር አባላት ከመምረጥና ከመመረጥ በስተቀር በሌሎች የአባልነት መብቶች ላይ ሁሉ እኩል ተጠቃሚ ናቸው:
5.3.3.ለኢትዮጵያ አገራዊ አንድነት የቆመና የተለያዩ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ክፍሎች ተባብረውና ተከባብረው በሰላም አብሮ መኖርን የሚቀበል ፣
5.4. በጀርመን ሃገር (በአውሮፓ) ዉስጥ በወንጀለኝነት የማይፈለግ ወይም በህገ ወጥ መንገድ ገንዘብ ከሚሰበስቡ ድርጅቶች ዉስጥ የማይሳተፍ፣ ተከሶ ያልተቀጣና በወንጀል የማይፈለግ (የማትፈለግ) በኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ አባል መሆን ይችላል(ትችላለች::
5.5.አንድ ሰዉ የማህበሩ አባል መሆን የሚችለው በማህበሩ ምስረታ ላይ ሲገኝ ወይም የአባልነት ቅጽ ሞልቶ ሲያመለክት ብቻ ነው:: የአባልነት ማመልከቻው ተሞልቶ ለማህበሩ ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በጽሁፍ መቅረብ አለበት:: አባልነቱ የሚረጋገጠው የማህበሩ የአመራር ኮሚቴ ወስኖ የማህበሩን ህገ ደንብ አባሪ አድርጎ በጽሁፍ ለአመልካቹ ሲልክለት ብቻ ነው:: የአባልነት ማመልከቻው ዉድቅ ከሆነ አመልካቹ ጽሁፉ በደረሰው በአንድ ወር የጊዜ ገደብ ውስጥ ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ይግባኝ ማቅረብ ይኖርበታል:: የአመራር አካሉ ማመልከቻውን ዉድቅ ያደረገበትን ምክንያት መስጠት አይገደድም:: የአመራር ኮሚቴው የይግባኙን በጽሁፍ ለሚከተለው የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል::

ኣንቀጽ 6 የእባላት መብት

6.1.ማንኛዉም ኣባል በማህበሩ ህገ ደንብ ዉስጥ የተደነገገለትን መብት መጠቀም ይችላል. በተለይም በጠቅላላ ጉባዔዉ ተካፍሎ በዉይይት አርእስቶች ላይ የመወሰን መብት ኣለዉ.
6.2.የማህበሩን የአመራር አካላት የመምረጥና በነሱ ዉስጥ የመመረጥ መብት አለው:: አባሉ በማናቸውም የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም በተለያዩ ማህበራት ወዘተ. የአመራር አካል ከሆነ በማህበሩ የአመራር ኮሚቴ ዉስጥ መመረጥ አይችልም::
6.3. ማንኛዉም አባል በማህበሩ ንብረቶች የመጠቀምና በማህበሩ የእንቅስቃሴ ህይዎት የመካፈል መብት አለው::
6.4.ማንኛዉም አባል የጠቅላላ ጉባዔና የስራ ኣስኪያጅ ኮሚቴ ዉሳኔዎችና ድንጋጌዎችን መዛግብት የማህበሩ ዋና ጸሃፊ በተገኘበት ማየትና ማንበብ ይችላል. መዛግብትንና መረጃዎችን ወስዶ በማራባት ለአባላትና አባል ላልሆኑ ግለሰቦች ማሰራጨት ግን በማህበሩና በጀርመን (የአውሮፓ) ህገ ደንብ መሰረት ፍጹም ክልክል ነው::
6.5. ማንኛውም አባል ማህበሩ ስበሳብውን የሚያካሂደበትንም ሆነ ወደ ድህረ ገፁ የመግቢያውን ቁልፍ ወይም( Password) የማህበሩ አባል ላልሆነ ሰው ሰጥቶ ቢገኝ አስተዳደራዊ እርምጃዎች ሊወሰድበት ይችላል::
6.6.ማንኛዉም አባል ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ሴሚናሮችና ኮንፈረንሶች ላይ በነጻ የመሳተፍ መብት አለው፣ ማህበሩ በሚያዘጋጃቸው ሴሚናሮችና ኮንፈረንሶች ላይ የስራ አመራሩ የመግቢያ ክፍያ ከተመነ ግን በነጻ የመሳተፉ መብት ውድቅ ይሆናል::

አንቀጽ 7 የኣባላት ግዴታ

ማንኛዉም አባል የሚከተሉትን ግዴታዎች ሟሟላት ይጠበቅበታል
7.1.የማህበሩን ህገደንብና ዉሳኔዎቹን ማክበር
7.2.የማህበሩን ዓላማዎች ማስፋፋትና ማጠናከር
7.3.የጠቅላላ ጉባዔና የአመራር ኣካል ዉሳኔዎችን ማክበርና በስራ ላይ ማዋል
7.4.የአባልነት መዋጮውን በወቅቱ መክፈል
7.5.የማህበሩን እንቅስቃሴዎች በትጋት መስራትና ማጠናከር

ኣንቀጽ 8 የኣባልነት መውጮ

8.1.ማንኛዉም አባል የማህበሩን የአባልነት ወርሃዊ መዋጮ የመክፈል ግዴታ አለበት. የመዋጮው መጠን በጠቅላላ ጉባዔው ተመርምሮ ከወቅቱ ጋር በማጣጣም ይወሰናል:: በኣሁኑ ጊዜ ወርሃዊ መዋጮዉ —€ የመመዝገቢያ ዋጋ ኣንድ ጊዜ —- € እንዲሆን ተወስኖአል.

8.2.የአባልነት መዋጮው ቢያንስ በ3 ወር ዉስጥ መከፈል አለበት:: የአባልነት ክፍያ በየግማሽ አመቱ ወይም በየአመቱ መክፈል ይቻላል:: መዋጮው ቢያንስ በ3ኛዉ ወር መጨረሻ ላይ መከፈል አለበት.

ኣንቀጽ 9 ከማህበሩ ኣባልነት ስለመውጣት

9.1. ማንኛውም አባል ከማህበሩ ኣባልነት በማንኛዉም ጊዜ መሰናበት ይችላል
9.2. አንድ አባል ከማህበሩ ሲሰናብት ከመሰናበቻው ቀን በፊት የ 4 ሳምንታት የጊዜ ገደብ ሰጥቶ
ለማህበሩ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ በጽሁፍ ማስታወቅ አለበት. የስንበት ደብዳቤው ህጋዊ የሚሆነው እስከ መሰናበቻ ቀኑ ድረስ ያለበትን የማህበሩን ወርሃዊ መዋጮ አጠቃሎ ሲከፍል ብቻ ነው
9.3.ማንኛዉም አባል የመሰናበቻ ጽሁፍ ሳያቀርብ በሌሎች ምክንያቶች ከማህበሩ ከወጣ ተመልሶ አባል ለመሆን ጥያቄ ካቀረበ በስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ታይቶ ይወሰናል::

ኣንቀጽ 10 ከማህበሩ ኣባልነት ስለመወገድ

10.1. ማንኛዉም አባል በሚከተሉት ምክንያቶች ከማህበሩ ሊወገድ ይችላል.
10.1.1 የማህበሩን ህገ-ደንብ ጥሶ የማህበሩን ጥቅምና እንቅስቃሴ የሚጻረር ተግባራትን መፈጸሙ በማስረጃ ሲረጋገጥበት
10.1.2 .በማህበሩ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሶ ሲገኝ
10.1.3. የመተዳደሪያ ደንቡን ተከትሎ: ግልፅነት በተሞላበት መልኩ በማህበሩ አባላት በድምጽ ብልጫ የሚጸድቁ ተግባራትን ባለመቀበል በስርአት አልበኝነት፣ ፀብ አጫሪነትና ረብሻ ብጥብጥ የሚያስነሳ ማንኛውም አባል ለአጭርም ሆነ ለረዥም ግዜ ከማህበሩ ሊታገድ ወይም ከማህበሩ ሊሰረዝ ይችላል::
10.1.4.እምነትን ሲያጎድልና ማህበሩን ያለአግባብ ሲጠቀምበት ሲገኝ
10.1.5.የወራት የአባልነት መዋጮውን ሳይከፍል ቀርቶ ሁለት ጊዜ ማስጠንቀቂየ ደርሶት ያለበትን ውዝፍ አጠቃሎ ካልከፈለ፣
10.1.6. ከዚህ አለም በሞት ሲለይ

ምዕራፍ አምስት

ኣንቀጽ 11 የማህበሩ የአመራር አካላት

ማህበሩ የሚከተሉት የሥራ አመራር አካላት አሉት
11.1. ጠቅላላ ጉባዔ
11.2. የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ
11.3. የሂሳብ መርማሪ (ኦዲተሮች) ኮሚቴ
11.5. የተለያዩ የንኡሳን ኮሚቴዎች

ኣንቀጽ 12 ጠቅላላ ጉባዔ

ጠቅላላ ጉባዔ የማህበሩ የበላይ አካል ሲሆን የሚከተሉትን ተግባራትን ያከናውናል

12.1. ከስራ አስኪያጅ ኮሚቴ የሚቀርቡትን የአመት በጀት ያጸድቃል፣ ይወስናል
12.2.የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አመታዊ የስራ ሪፖርት ያዳምጣል የስራ አፈጻጸማቸውን ይገመግማል መመሪያ ይሰጣል::
12.3. የስራ አስኪያጅ ኮሚቴን ያሰናብታል
12.4. ወቅቱን የተከተለ የአባልትን ወርሃዊ መዋጮና የመመዝገቢያ ተመን ይወስናል.
12.5. የስራ አስኪያጅ፣የቁጥጥር ና የሂሳብ መርማሪ ኮሚቴ አባላትን (ኦዲተሮችን) ይመርጣል.
12.6. የአባልነት ማመልከቻቸዉ ዉድቅ የሆኑ ኣመልካቾች ይግባኝ ላይ ዉሳኔ ይሰጣል.
12-7..ማህበሩ በኢትዮጵያ ለሚደርሱ የተፈጥሮ ሰው ሰራሽ አደጋዎች የሚሰጠዉን የእርዳታና የድጋፍ መጠን ይውስናል

ኣንቀጽ 13 የጠቅላላ ጉባዔ ኣጠራርና ዉሳኔ አሰጣጥ

13. የጠቅላላ ጉባአዔ ዉሳኔ በአንድ ድምጽ ብልጫ ይጸድቃል.

13.1. የማህበሩ ጉባዔ ድምጽ አሰጣጥ እኩል ከሆነ ሰብሳቢው የደገፈው ውሳኔ ተፈጻሚነት ይኖረዋል::
13.2.የማህበሩን ህገ ደንብ ለመለወጥና ማህበሩን ላማፍረስ ግን በኣባልት ¾ ድምጽ መደገፍ አለበት::
13.3. የአባላቱ 1/10 ኛ የማህበሩ አባላት ምክንያታቸዉን ገልጸዉ ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ በጽሁፍ ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ከአቀረቡ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አስቸኳይ የጠቅላላ ጉባዔ መጥራት አለበት
13.4. መደበኛዉ ጠቅላላ የአባላት ጉባዔ በ ዓመት አንዴ ይሆናል:: ኣስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በግማሽ አመት ነሃሴ ውስጥ ይጠራል::
13.5.የጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ቀን ቦታና ሰዓት ተጠቅሶ የስበሰባዉ ቀን፣ ከመድረሱ 30 ቀናት በፊት የጥሪ ደብዳቤዉ በሥራ አስኪያጅ ኮሚቴው ለአባላት በሙሉ በቅድሚያ መላክ አለበት.

ኣንቀጽ 14 የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ

14.1.የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ለማናቸዉም የማህበሩ የስራ እንቅስቃሴ ሃላፊነቱ በህገ ደንቡ ለሌላ የአመራር አካላት እስካልተሰጠ ድረስ ተጠያቂ ነዉ:: በተለይም የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፣የውይይት አርእስቶችን ዘርዝሮ ለጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ አባላትን ይጠራል
14.2.የጠቅላላ ጉባዔ ዉሳኔዎችን ተግባራዊ ያደርጋል
14.3. በማህብሩ ሕገ ደንብ የጸደቁ ዓላማዎች ተግባራዊ ለማድረግ እቅድና ፕላን በማውጣት ተግባራዊ ያደርጋል አፈጻጸማቸውን ለጠቅላላ ጉባኤው ሪፖርት ያቀርባል.
14.4.የማህበሩን አመታዊ ባጀት ነድፎ ለጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል. በማህበሩ የገንዘብ ሁኔታና በማህበሩ እንቅስቃሴ ላይ አመታዊ ሪፖርት ያቀርባል.
14.5.በአዲስ አባላት የአባልነት ማመልካቻዎች ላይ ዉሳኔ ይሰጣል
14.6.ማህበሩ በሚያዘጋጃቸዉ ሴሚናሮችና ኮንፈረንሶች የመግቢያ ክፍያ ጣራ ይወስናል
14.7.አጣዳፊ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን ብማሰባሰብ ይተነትናል የፕሬስ መግለጫዎችን ያወጣል ፣ያሰራጫል
14.8. ከተለያዩ ተቋማት ጋር ይገናኛል፣ ትብብር ይፈጥራል፣ ውል ይፈራረማል በጠቅላላ ጉባዔው የሚሰጡ መመሪያዎችንና ውሳኔዎች ያስፈጽማል::
14.9.በስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ የሚወሰነዉ ውሳኔ ህጋዊ የሚሆነዉ(ምልዓተ ጉባዔ) የአመራሩ አባላት ከግማሽ በላይ ሲገኙ ብቻ ነው::
14.10. የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ በጠቅላላ ጉባዔዉ ለ 1 የስራ ዘመን ይመረጣል. አንድ የስራ ዘመን 2 አመት ነው::
14.11. የማህበሩ አመራሮች የስራ ዘመን ሲያበቃ አዲስ ምርጫ የሚያስፈጽሙ ሶስት አስመራጭ ኮሚተ አባላት በጠቅላላ ጉባዔው ይመረጣሉ ::
14.12. ማንኛዉም የኣመራር አባል በተከታታይ ለሁለት የስራ ዘመናት መመረጥ ይችላል.
14.13. ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባልነት የሚወዳደሩት እጩዎች ከምርጫዉ በፊት በምርጫዉ ለመሳተፍና ላለመሳተፍ ፈቃደኝነታቸዉን ለአስመራጭ ኮሚቴ በቅድሚያ ማረጋገጥ አለባቸዉ. የድምጽ አሰጣጡ እጅ በማንሳት ይሆናል እያንዳንዱ የስራ ሃላፊነት የሚወሰነዉ በጠቅላላ ጉባአዔ ነው::

ኣንቀጽ 15 የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት

15.1. የሥራ አሥኪያጅ ኮሚቴ በአንቀጽ§26 BGB በጠቅላላ ጉባአዔ ከሚመረጡት 7 አባላት ያሉት ይሆናል:፣ሶስት(3) የሥራ ስኪያጅ ኮሚቴ አባላት በጋራ ማህበሩን በህግ ፊትና ከህግ ፊት ዉጪ ይወክላሉ፣ ሊቀመንበሩ ኦፊሲዬላዊ የማህበሪ ተጠሪ ነው ::
15.2. የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴው ሊቀመንበር ምክትል ሊቀመንበር፣ ፀሃፊ አቃቤንዋይ(ገንዘብያዥ)፣የሒሳብ ሹም፣ የህዝብግንኙነትሃላፊ፣የሚዲያና የማስታወቂያ ኦፕሬሽን አገልግሎት፣ያሉበት ባለሰባት የስራአስኪያጅ ኮሚቴ ያቋቁማል፡፡
15.3.1ለስራው ክንውን የሚረዱ የስራ አፈጻጸም ስርዓቶች ያሰናዳል።በጠቅላላ ጉባዔው ሲጸድቅም በስራ ላይ ይውላል።
15.4. የማህበሩን ስራ ለማከናወን አስፈላጊ የሆኑ ንዑሳን ኮሚቴዎች ያቋቁማል፣መመሪያ ያወጣል፣መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
15.5. እንደ አስፈላጊነቱ በየጊዜው አየተገናኘ መደበኛ ስራውን ያከናውናል።
15.6. ለጠቅላላ ጉባዔ የስራ ክንውን ዘገባ በተወሰነ ጊዜ ያቀርባል።ግንኙነቱ በአካል: በቴሊ ኮንፈረስ በምስል(Video Conference) በድምጽ ግንኑነት መስመሮች ( voice room conferences) ይሆናል
15.7. ለማህበሩ ገቢ ያሰባስባል።
15.8. ቅጾችን አዘጋጅቶ ስራ ላይ ያውላል:
15.9 በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት እርዳታ ይሰጣል።
15.10 አስፈላጊ ኢንፎርሜሽን ለአባላት በወቅቱ አንዲደርስ ያደርጋል።
15..11 የማህበሩን ገንዘብና ንብረት በአግባቡ ይይዛል።
15..12 የማህበሩ አሰራር የሚሻሻልበት መንገድ እያጠና በቦርድ ሲፈቀድ ስራ ላይ ያውላል።

16.የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ ተግባርና ስልጣን

ሰባቱ የስራአስኪያጅ ኮሚቴ አባላት የሚከተሉት ተግባራትና ስልጣን ይኖራቸዋል።

16.1 ሊቀመንበር፣

16.1.1. የጠቅላላ ጉባዔውንና የሥራ አስኪያጅ ኮሚቴ ስብሰባ በሊቀ-መንበርነትይመራል።
16.1.2 የማህበሩ ስራ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት አንዲከናወን ያቅዳል፣የማህበሩን ስራይመራል፣አባላትንያስተባብራል፣ይቆጣጠራል።
15.1.3 በየጊዜው ለሚደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ስብሰባ የስራ ክንውን ዘገባ ያቀርባል።
16.1.4.የስራ አስኪያጅን ስብሰባ ይጠራል፣አስቸኳይ ሁኔታ ከአጋጠመ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሃሳብ ያቀርባል።
16.1.5 የወጪ ማዘዣዎችንና ደብዳቤዎችን በማህበሩ ስም ይፈርማል።

16..2 ምክትል ሊቀመንበር፣

16.2.1 ሊቀመንበሩ የማይገኝበት ጊዜ ሊቀመንበሩን ተክቶየ ማህበሩን ስራ ያከናውናል።
16.2.2.ከሊቀመንበሩ ጋር በመሆን ማህበሩን ይወክላሉ::
16.2.3.ከሥራ አስኪያጅ ኮሚቴውና ከሊቀመንበሩ የሚሰጡትን ተጨማሪ ስራዎች ያከናውናል::

16.3 ጸሐፊ

16.3.1 የማህሩን አባላት የስም ዝርዝርና መዛግብት ይይዛል።
16.3.2የጠቅላላ ጉባዔውንና የስራ አስኪያጅ ኮሚቴውን አጀንዳ አዘጋጅቶ ሊቀመንበሩ ሲፈቅድ በየወሩ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባሎችን፣በየሶስት ወር፣ ሲወሰን የማህበሩ ጠቅላላ ስብሰባ ይጠራል።
16.3.3 የስብሰባዎችን ቃለጉባኤ ይይዛል፣ያዘጋጃል፣ለስራ አስኪያጅ ኮሚቴው ያቀርባል።
16.3.4 የማህበሩን ጽህፈት ቤት ስራ ያከናውናል።

16.4 ገንዘብ ያዥ

16.4.1.1በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት ለማህበሩ ገቢ ሊሆን የሚገባውን ገንዘብበ የጊዜው እየሰበሰበ በማህበሩ የባንክ ሂሳብ ያስቀምጣል።
164.2 በመመሪያው መሰረት ማህበሩ ለአባሎች የሚሰጠውን ዕርዳታ ወይም ክፍያ ቦርዱ ሲወስን ይፈጽማል።
16.4.3 ቼኮች በሁለት ስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባሎች መፈረማቸውን ያረጋግጣል፡፡
16.4.4 የማህበሩን ስራ ማካሄጃ በጀትያዘጋጃል፣ሲጸድቅም በስራ ላይ ያውላል።
16.4.5 ወጪዎቹ በበጀት ከተፈቀደው በላይ አለመሆናቸውን ይከታተላል።

16.5 የሂሳብ ሹም (አካውንታንት)
165.1 የማህበሩን የሂሳብ መዛግብት ይይዛል።
165.2 የማህበሩን የገቢና የወጪ ደረሰኞች ይይዛል።
16.5.3 ገቢዎች በአግባቡ የተሰበሰቡ መሆኑን መርምሮ ያረጋግጣል።
16.5.4 የባንክ ደብተሮች ይይዛል፣
5.5.5.5 የማህበሩን ሂሳብ ሪፖርት ያዘጋጃል፣ያቀርባል።
16.5.6 በመንግስት ተቋማት የሚጠየቅ የሂሳብና የታክስ ሪፖርት ያዘጋጃል።

16.6 የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ

16.6.1.1በማንኛውም ማህበሩን በሚመለከት ሁኔታ የሚደረገውን የማሰተዋወቅያ ስራ ያከናውናል።
16.6.2 ከተለያዩ ተመሳሳይ ዓላማ ያላቸው ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ይመሰርታል።
16.6.3 ማህበሩን ለማስተዋወቅና ለማሳደግ የሚረዱ ጽሁፎችን አያዘጋጀ በየቦታው ይበትናል።
16.6.4 ማንኛውንም የማህበሩን ጉዳይ በተመለከተ አስፈላጊውን መረጃ ለአባላት ያስተላልፋል ወይም መተላለፉን ያረጋግጣል።
16.6.5 የማህበሩን ዓላማ ሊያግዝ ከሚችሉ ተቋማት ሊገኝ የሚችለውን ጥቅምና እርዳታ እየተከታተለ ለስራ አስኪያጅ ኪሚቴው ያቀርባል።
16.6.6.የማህበሩን ዓላማ ለማስፈጸም ከሚያግዙ ተቋማት ጋር ግንኙነት በመመስረት ስለ ዝርዝር ስራቸው ለሥራ አስኪያጅ ኮሚቴው ሪፖርት በማቅረብ ማህበሩ በተሻለ ሁኔታ አገልግሎቶች የሚያገኝበትን መንገድ ያዘጋጃል።

16.7 የማስታወቂያና ኦፕሬሽን አገልግሎት ሃላፊ

16.7.1.የማህበሩ አሰራር በሚቀላጠፍበት ሁኔታላይ አጠቃላይ ጥናቶችን እያደረገ ሪፖርቱን ያቀርባል በማህበሩ የዶሜይን(Domain) ድረገጽ(website) ይለጥፋል ።
16.7.2.ስለ ስብሰባ ቦታዎችና አጀንዳዎች፣ትራንስፖርት፣ፓሊስ፣እና ሰለመሳሰሉት ከማህሩ ስራ ጋር ሰለሚገናኙ ተቋማትና አገልግሎቶች አስፈላጊውን ጥናትና ክንውን ሪፖርት ለሥራ አስኪያጅ ኪሚቴውና አስፈላጊም ከሆነ ለአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ያቀርባል።
16.7.3.ማህበሩ ከጋራ ዋስትና ወይም መድሕን ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ አጥንቶ ለቦርዱ ሪፖርትያቀርባል።
16.7.4.የማህበሩን ዓላማ ለማስፈጸም ያግዛሉ ተብለው የሚገመቱ ኮሚቴዎችን አዕዲቶሪያል ቦርዶችን የማቋቋም ጥረቱን በሃላፊነት ይመራል።
16.7.5.ማህበሩሕጋዊ አካልነት ለማግኘትና ይህን ይዞ ለመቆየት የሚያስፈልገውን ሁኔታ በመከታተል ስራ ላይ ያውላል።
16.7.6. የማህበሩን ድህረ-ገጽ የማቋቋሙን፣የማስተደደሩንና የማሳደጉን ጥረት በኃላፊነትይመራል።
16.7.7. የማህበሩን የ Domain (ድረገጽ) ስምያስመዘግባል፣ምዝገባውም አንዳያልፍበት በየዓመቱ አስፈላጊውን ዕድሳት ያደርጋል።
16.7.8..አባላት የማህበሩን ድህረገጽ በሚገባ የሚጠቀሙበትን ሁኔታ እያጠና ለሰራ አስኪያጅ ኮሚቴው በማቅረብ ጥናቶችን ስራ ላይ ያውላል።

17.1.ኦዲተር

17.1.ከጠቅላላ ጉባኤው ጉባዔው ይመጥናሉ የሚባሉትን ሶስት አባላት መርጦ ኦዲተር ይሰይማል።
17.2 ኦዲተሩ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባዔው ይሆናል።
17.3 ኦዲተሩ በሂሳብ ባለሙያው ተዘጅቶ የቀረበውን ዓመታዊ ሪፓርት መርምሮ የደረሰበትን ለጠቅላላ ጉባዔው ያቀርባል።
17.4. ጠቅላላ ጉባዔው አስፈላጊ ሆኖ ካገኘው ኦዲተር ሙሉውን ዓመት የሚያጠቃልል፣የወራት፣የሩብ ዓመት፣ወይም የግማሽ ዓመታት ሪፖርቶችን እንዲያቀርብ ሊጠይቅ ይችላል።

ምዕራፍ አምስት

18. የማህበሩ የስራ ቋንቋዎች
18.1. የማህበሩ የሥራ ቋንቋዎች አማርኛ፣ እንግሊዝኛና ጀርመንኛ ይሆናሉ::

ኣንቀጽ 19. የጠቅላላ ጉባዔ ሪፖርት

19.1.የጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ሪፖርት በጸሃፊው ይያዛል. በስብሰባው መጨረሻ ላይ ተጠናቅሮ ከቀረበና ለጠቅላላ ጉባዔ ከተነበበ በኋላ በሊቀመንበሩና በጸሃፊው ይፈረምበታል::

ኣንቀጽ 20. የዘመን አቆጣጠር

20.1. የማህበሩ የሰራ ዘመን የሚቆጠረው በአዉሮፓውያን የሰራ ዘመን ይሆናል.

ኣንቀጽ 21. ማህበሩን ስለማፍረስ

21.1. በማህበሩ የአባላት ጠቅላላ ጉባዔ ተመክሮ ውሳኔ ላይ ከተደረሰ በህገደንብ አንቀጽ 13.2. መሰረት ሊፈርስ ይችላል.
21.2. ማህበሩ ሲፈርስ ወይም የማህበሩ አላማ ከህገ ደንቡ ዉጪ ሲሆን የማህበሩ ንብረት በጀርመን ሃገር ዉስጥ በሚገኘው የ_____________ ድርጅት በኩል በአዲስ አበባ ለሚገኘው ___________ ድርጅት ይተላለፋል::

22. የማህበሩሕገ-ደንብ(Bylaw)
22.1.ይህ ሕገ-ደንብ የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ ሕገ ደንብ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

ኣንቀጽ 23. ሕጉ የሚጸናበት ጊዜ

23.1.ይህ የመተዳደሪያ ደንብ በጠቅላላ ጉባዔ ተወስኖ በጀርመን(የአውሮፓ አህጉር) የአስተዳደር ፍ/ቤት ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ይሆናል::

__________________ City
…………………….. June 2020

የኢትዮጵያውያን ማህበር በአውሮፓ

About expeder

Check Also

ከኢትዮጵያዉያን ማህበር በአዉሮፓ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

PressRelease-AMHARIC- by A.E.E-March 23-2024

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

− 1 = 1